በተለይም በአሁኑ ሰዓት ፈተና ላይ የጣለን የምርጫ ጉዳይ እንደምናሸነፍ ቃል የተያዘበት ቢሆንም [ቃለ ጉባዔ/የፓርቲው ሊቀመንበር መመሪያ?]፤ ፈተናዎች የሚፈጠሩት በሕዝብ እና በራሱ ታማኝ ባልሆኑ ሃይሎች ማለትም በመንግሥት ክንፍ አይቀለበስም ብሎ ማሰብ አይቻልም፡፡ በዚህም ቀድሞ መዘጋጀት ያለበት እና ለሁከት እና ለብጥብጥ መሳሪያ ሊሆን የሚችለው የሕዝብ ክንፍ የተማረው ሃይል ሊሆን ስለሚችል ሊታሰብ ይገባል ብለዋል [የፓርቲው ሊቀመንበር?]፡፡”
“[አደራጃጀታችን] ከምንም በላይ የብጥብጥ እና የሁከት መንስኤ የሆነውን ተማሪ በኢሕአዴግ አመራር አባላት እየታገዘ ለመያዝ የሚያስችል ነው፡፡ በምርጫው ሊፈጠር የሚችለውን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሁከት እና ብጥብጥ፤ ለማሰቆም በማደራጀት፤ መረጃ በመጥለፍ አመችነቱ የላቀ እንደሚሆን ታምኖበታል፡፡”
– “በመሆኑም ሁለቱም የሰራዊቱ ክንፍች [የሕዝብና መንግሥታዊ/ፓርቲ] በሙሉ በምርጫው ዘሪያ በቂ ግንዚቤ እንዲጨብጡ ማዴረግ፣ ተገቢውን አደረጃጃትና አሰራር ዘርግቶ መላው መካከለኛ አመራር፤ ዝቅተኛ አመራር፤ መምህራን፤ የምርምር አካላት፤ ድጋፍ ሰጭ ሰራተኛና ተማሪዎች ግልጽ ስምሪት መስጠት፣ ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ በቀጣይነት በማድረግ እያንዲንዱ የሠራዊት ድጋፍ ክንፍ ወደ ሚፈለግበት የጥንካሬ ደረጃ እየደረሰ መሆኑንና የተቋሙ ዕቅድ በውጤታማነት መፈፀሙን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል፡፡”
– “… ሁለም የዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንቶች ውጤታቸው የሚሞላላቸው ለምርጫው በሚያዘጋጁት የድጋፍ ኃይል ይወሰናል፡፡”
– “… ሁለም የዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንቶች ውጤታቸው የሚሞላላቸው ለምርጫው በሚያዘጋጁት የድጋፍ ኃይል ይወሰናል፡፡”
ምንጭ፡ በትምህርት ሚኒስትሩ ሽፈራው ሽጉጤ አስተባባሪነት የተዘጋጀው:
“የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኢሕአዴግ የምርጫ ድል ልማት ሠራዊት ግንባታ አድረጃጀት ማንዋል – ለምርጫ 2007”
ማጠቃለያ
ራሱ ሕወሃት/ኢሕአዴግም እንዳመነው፡ በከፍተኛ ፍርሃት እየራደ ያለ ባለአራት-ግንባሮችና ሌሎች አናሳ ቡድኖች ስብስብ ዋናው ሥልጣን በሕወሃት እጅ ሆኖ በኃይልና በከፍተኛ ጭቆና ሃገራችንን የሚያስተዳድር የፖለቲካ ድርጅት ነው። ከባህሪው የድርጅቱ ትልቁ ችግርም፡ ሣር ቅጠሉ ሳይቀር፡ ከዛሬ ነገ ሥልጣን ያሳጡኛል ብሎ በሥጋት የሚኖር በመሆኑ፡ ሣሩ፡ ቅጠሉንና ጎመኑም ጠላቶቹ እየመሰሉት፡ በእስር ቤት የሚያጉራቸው ወገኖቻችንን ብዛት ቤቶቻቸው ይቁጠሯቸው ብሎ ማለፉ፡ በቆጠራ ብቻ ጊዜ ከማባከን ያድናል።
ከላይ የተቀመጡት የፖለቲካ ድርጅቱን አስተሳሰብና ማንነት የሚጠቁሙት ጥቅሶች እንደሚያመለክቱት፡ ሌላው ቀርቶ፡ መከላከያውና የስለላው ዘርፍ ሃገር በሚያስተዳድርበት ሁኔታ እንኳ፡ አገዛዙ “በሕዝብ እና በራሱ ታማኝ ባልሆኑ ሃይሎች ማለትም በመንግሥት ክንፍ አይቀለበስም ብሎ ማሰብ አይቻልም” በማለት ስለመጭው ምርጫ ያለውን ሥጋት ያረጋግጥልናል፡፡
ከላይ የተቀመጡት የፖለቲካ ድርጅቱን አስተሳሰብና ማንነት የሚጠቁሙት ጥቅሶች እንደሚያመለክቱት፡ ሌላው ቀርቶ፡ መከላከያውና የስለላው ዘርፍ ሃገር በሚያስተዳድርበት ሁኔታ እንኳ፡ አገዛዙ “በሕዝብ እና በራሱ ታማኝ ባልሆኑ ሃይሎች ማለትም በመንግሥት ክንፍ አይቀለበስም ብሎ ማሰብ አይቻልም” በማለት ስለመጭው ምርጫ ያለውን ሥጋት ያረጋግጥልናል፡፡
በታሪክ እንደታየው፡ አንዳንድ መሪዎችና መንግሥታትም በውናቸውና በእንቅልፋቸው ጠላት ካልፈጠሩ ሥራቸውን መሥራት እንደሚያስቸግራቸው ሁሉ፡ ዛሬ ሕወሃት/ኢሕአዴግም ክፉኛ እየተረበሽ በመሆኑ፡ ኢትዮጵያ ውስጥና ከኢትዮጵያ ባሻገርም እስትንፋስ ያለው ነገር ሁሉ ‘እያሴረብኝ ነው፤ ጠላቴ ነው’ ብሎ የሚያምንበት ደረጃ ላይ ይገኛል።
ይህ ‘መንግሥታዊ’ መሸበር ምን ያህል ሃገራችንንና ሕዝባችንን ይጎዳ ይሆን? ከዚህ በፊት እንዳደረገው ሁሉ፡ ይህ ሁኔታው የሚያስከትለው የሉዓላዊነት ሽያጭና ምንዘራ ይኖር ይሆን? በምርጫ ታኮ፣ ለብዙዎች ሕይወትስ መቀጠፍ እንደገና ሁኔታውን ያመቻች ይሆን? ቀደም ብለው በፖለቲካ ድርጅቱ የተጀመሩት ዝግጅቶች ይህንኑ በገሃድ የሚያመላክቱ ስለሆኑ፡ ለጥያቄዎቹ የኔም መልሴ የእነዚህ ሁኔታዎች ተፈጻሚነት ዕድሎች ካለመሆን ይልቅ ወደ መሆን ያመዝናሉ የሚል ነው!
እነዚህም ድርጊቶቹ በሕግጋት ጥሰት የተሞሉ በመሆናቸው፡-
(ሀ) የምርጫውን ውጤት ከምርጫው በፊት በመተንበይና ውጤቱም በኃይል አጠቃቀም፡ ለሕወሃት/ኢሕአዴግ እንዲመቻች መደረጉን በመረጃነት በመያዝ፤
(ለ) የሀገሪቱን ዜጎች (ወጣቶች፡ ተማሪዎች፡ ምሁራን፡ አብዛኛውን ሕዝብና ቢሮክራሲውን ወዘተ) በመለየት ለጥቃት እያዘጋጀ ሕዝቡንም ወደ እርስ በእርስ ግጭት እየገፋፋ በመሆኑ፤
(ሐ) ከአመራር በማይጠበቅ የማጭበርበርና ሌሎችም ሕገወጥ ተግባሮች፡ ለምሳሌ የሕዝብን የግብር ክፍያ ለራሱ የፖለቲካ ጥቅም የማዋል ወንጀሎች መፈጸሙን በማስመልከት ዜጎች መረጃውን ለሕዝብ እንዲጋለጥ ማድረጋቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያምም ይህንን ሕገወጥ ድርጊት ሕጋዊ ነው በማለት ባለፈው ጥቅምት፡ ፓርላማ ውስጥ አቋማቸውን ማሳወቃቸው ይታወሳል!
(መ) ወጣት ተማሪዎቻችን በሥነ ሥርዓት ትምህርታቸውን በመከታተል ዕውቀት ቀስመው ሃገራቸውን ወደፊት ለማስገስገስ እንዳይችሉ፡ ትምህርት ቤቶችን ለስለላና ለርዕዮተ ዓለም ማስፋፊያ በመጠቀሙ፣ በቤተስብና በትምህርት ቤቶች ዙሪያ የምሥራቅ ጀርመን የስለላ ድርጅት ስታዚ በተጠቀመበት አንድ ለአምስት የስለላ አሠራር ቤተስቦችንና ሠራተኞችን በየፊናቸው አቆላልፎ (“The Stasi Octopus”) የግለስቦችን ነጻነትና ደህንነት በማናጋቱ፡ ለሰብዓዊ ክብር መዋረድና ለትምህርት ጥራት ጉድለት ሕወሃት/ኢሕአዴግ ተጠያቂ ሊደረግ ይገባል።
የወቅቱ አሳሳቢ ሥዕል
ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ በርከት ያሉ ጸረ-ወጣቶች፣ ጸረ-ተማሪዎችና ጸረ-ምሁራን፣ የትምህርት ጥራትን አዳፋኝ የሆኑ፡ ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋትን ብቁ የሰው ኃይል እንዳታፈራ የዘለቄታ መንገዷን የሚያደናቅፉ ድርጊቶችና በአመራር አካላት የተዘጋጁ ጽሁፎች – አንዳንዴም እንደ ሕወሃት/ኢሕአዴግ ጥናቶች ሌላ ጊዜ ደግሞ መመሪያዎች እየተባሉ – ገዥው ፓርቲ በቀጥታና በሚስጢር ለአባሎቹ ሲያሠራጭ ከርሟል። ይዘቶቻቸውም ሆነ ተጽዕኖዋቸው (impact) ምን እንደሆነ ለመረዳት ኮሜት ላይ ሮኬት ለማሳረፍ የሚያስችል ዕውቀት አይጠይቅም።
በተጨማሪም አንዳንድ ምንጮች (የዓለም አቀፍ ድርጅቶች መረጃዎችን ጨምሮ)፣ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የሚካሄዷቸው ጥናቶችና በዚህ ረገድ የውጭ ኤምባሲዎች የሚያስተላልፏቸው መረጃዎች በአንዳንድ አነስ ያሉ ትምህርት ነክ የሆኑ የፖሊሲ ስብሰባዎች አሜሪካና አውሮፓ ውስጥ አልፎ አልፎ ቀርበው፡ ለግንዛቤዎች ሠፊ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። እንዲሁም በየወቅቱና በየደረጃው በመነሻነት ወቅታዊ መረጃዎችንና የአገዛዙን አስተሳሰብ ስለሚያመላክቱ አሠራሮችና እርምጃዎችና ብዙ ጉዳዮች በኢሳት አማካይነትም ተደምጠዋል።
አሁን በያዝነው ወር “የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኢሕአዴግ የምርጫ ድል ልማት ሠራዊት ግንባታ አድረጃጀት ማንዋል – ለምርጫ 2007” የተሰኘ ጽሁፍ ቀርቧል – እነርሱ ማንዋል ይሉታል። ‘ማንዋሉ’ በተማሪዎች ሥልጠና ወቅት እንደተፈለገው አልደረሰም። በተደጋጋሚ ታሽቶና ተፈትጎ ቢቀርብም፡ አሁንም ይዘቱ በቀረበበት መልኩ ጥቅም ላይ ሊውል የማይችል በባዶ የካድሬ ቃላት ክምችት የተሞላ ስካር፡ ዓላማው ግን ምርጫውን እንዴት ሕወሃት/ኢሕአዴግ አሸናፊ እንዲሆን ማስቻል በመሆኑ፡ እንደገና እንዲፈተግና ካልጸዳ ሽንፍላነቱ እንዲላቀቅ በሌሎች እንዲሻሻል ተደርጎ እንደገና ጥቅምት 2007 ቢቀርብም፡ ለአባላት እንኳ እንዲበተን ፈቃድ ያገኘው ከብዙ ማመንታት በኋላ ኅዳር 2007 ነው።
ያንን የተዘጋጀውን ‘ማንዋል’ ለማንበብ ዕድል በማግኘቴ እንደ አንድ ምሁር፡ በግልጽነት ልለው የምችለውና ካሰመርኩባቸው ጉዳዮች ይዘቶቹ መካከል ለተማሪዎችና ምሁራን ያዘለው ሊገነፍል የደረሰ ጥላቻና ቂም በቀል ግንባር ቀደም ሆነው ታይተውኛል። ከሁሉም የከፋ – ከምርጫ ማጭበርበር ባሻገር – በምርጫው ሰሞን ስለሚሚቀጠቀጡት፡ በአፈሳ ስለሚታሠሩት ወይንም ሊገደሉ ስለሚችሉ ወጣቶች ሚኒስትሩና ግብረ አበሮቻቸው ከወዲሁ ተጠያቂ ሊደረጉበት የሚገባ፡ አፈናና ግድያ እንዲካሄድ መመሪያ የሚሠጥ ሠነድ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
ምንም እንኳ ሃገራችን በዘመነ ሕወሃት/ኢሕአዴግ 31 ያህል ዩኒቨርሲቲዎች እንዲኖራት ቢደረግም፡ ብዛት የጥራት መለኪያ ሊሆን ስለማይችል፥ በ2014 እና በ2013 ጽሁፎቼ፡ እነዚህ የከፍተኛ ትምህርቶች ተቋሞች ከዕውቀት ምንጭነት ይልቅ፡ ለሕወሃት የፕሮፓጋንዳ ማጥመጃ መረቦች መሆናቸውን ከማውቀውና ከሥጋቴ በመነሳት ችግሩን አስመልከቶ ሃሣቤን ለማካፈል ሞክሬያለሁ (http://ethiopiaobservatory.com/2014/08/20/2014-performance-ranking-of-ethiopias-31-universities-an-old-nation-being-reduced-to-beginner/ እና http://ethiopiaobservatory.com/2014/01/11/2013-performance-ranking-of-ethiopian-universities-in-both-african-and-global-metrics/)። ከትምህርቴና ከተለያዩ የሥራ መስኮች ከተቀስሙ ልምዶችና ግንዛቤዎች በመነሳት፡ በእነዚህ ጽሁፎችና በተያያዙ በሌሎችም አማክይነት (ለምሳሌም ያህል፡ Improving Education Quality, Equity and ACCESS
in Ethiopia፤ Education under persistent attack in Ethiopia፤ በቅርቡ ደግሞ What a time, when education is openly made instrument for rights violation with TPLF requiring ‘certificate’ of support for its policies for entry to college ወዘተ) ለማሰማት የሞከርኩት ነገር ቢኖር፡ የሃገራችን ዩኒቨርሲቲዎችና የተማረ የሰው ኃይል ምርቶቻቸው በአሁኑ አያያዛቸው፡ ከዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ይቅርና፤ ኋላቀር ነው በሚባለው ሠሃራዊው አፍሪካ ውስጥ ከሚገኙ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጅች ጋር እንኳ ሃገራችን ተወዳዳሪ መሆን እንደተሳናት ነው።
ምንም እንኳ ሃገራችን በዘመነ ሕወሃት/ኢሕአዴግ 31 ያህል ዩኒቨርሲቲዎች እንዲኖራት ቢደረግም፡ ብዛት የጥራት መለኪያ ሊሆን ስለማይችል፥ በ2014 እና በ2013 ጽሁፎቼ፡ እነዚህ የከፍተኛ ትምህርቶች ተቋሞች ከዕውቀት ምንጭነት ይልቅ፡ ለሕወሃት የፕሮፓጋንዳ ማጥመጃ መረቦች መሆናቸውን ከማውቀውና ከሥጋቴ በመነሳት ችግሩን አስመልከቶ ሃሣቤን ለማካፈል ሞክሬያለሁ (http://ethiopiaobservatory.com/2014/08/20/2014-performance-ranking-of-ethiopias-31-universities-an-old-nation-being-reduced-to-beginner/ እና http://ethiopiaobservatory.com/2014/01/11/2013-performance-ranking-of-ethiopian-universities-in-both-african-and-global-metrics/)። ከትምህርቴና ከተለያዩ የሥራ መስኮች ከተቀስሙ ልምዶችና ግንዛቤዎች በመነሳት፡ በእነዚህ ጽሁፎችና በተያያዙ በሌሎችም አማክይነት (ለምሳሌም ያህል፡ Improving Education Quality, Equity and ACCESS

ሁኔታዎች እንደሚያመላክቱትም ከሆነ፡ ችግሩ ከፖለቲካዊና ከአመራር ድንቁርናና ድህነት የመነጨ በመሆኑ፡ ለወደፊት እየተባባስ እንደሚሄድ ነው የሚተነበየው። ስለሆነም ለተረከበው ሃላፊነቱ ተጠያቂ የሚሆን መንግሥት እስኪመጣ ድረስ፡ ችግሩ ‘በነፕሮፌሰሮች’ ኃይለማርያም ደሳለኝ፡ ሽፈራው ሽጉጤ፡ በረከት ስምኦን፡ አባይ ፀሐዬ፡ ቴድሮስ አድሃኖም ወዘተ፡ የግልና የቡድን ሥልጣን ጥማት በተሳከሩና በጥቅም አሠራር በተመሠረተ አካሄድና አያያዛቸው የሚቀረፍ አይደለም።
በተለይም፡ ዩኒቨርስቲን የሚያህል ነገር፡ ያውም የዩኒቨርሲቲዎቹ ሴኔቶች በሕግ የተሰጣቸውን ሥልጣን በመጠቀም እርምጃ ሊወስዱ ሲገባ፡ (የሌላቸው ዩኒቨርሲቲዎቹም እንዲኖራችው በማድረግ) እንደ ትምህርት ሚኒስቴር ባለ ኋላቀር መሥሪያ ቤት ሥር ለተራ ጉዳዮች እንኳ አራት ኪሎ ማንኳኳትና ደጅ ጥናት የሚያስፈልግበት አስገዳጅ ሁኔታ – ተደርጎ በማይታወቅ አሠራር – በተለይም ስለ አስተዳደሩ፣ ሥራ ካሌንደሩና ካሪኩለሙ ምንም ዐይነት ስሜት፣ ብቃትና ግንዛቤ በሌለው/በሌላቸው ግለሰቦች እንዲመራ መደረጉ አንዱ የችግሩ ምንጭ ነው።፡
መለስ ብለን እንኳ ስንመለከት፡ የአማራ ብሄረስብን አባሎች ሃገራቸው ውስጥ በፈቀዱት አካባቢ የመኖር ሕጋዊ መብት የሌላቸው ዜጎች በማስመሰል በፊርማው ከጉራ ፈርዳ ባባረረ ግለስብ መዳፍ ሥር የሃገሪቱ የትምህርት ፖሊሲ አተገባበርና አፈጻጸም ከመውደቁ በላይ ለዕውቀት ውርደትና ለሃገራችንም ዘለቄታ ከዚህ የከፋ ነገር የለም።
በሌላ በኩል ደግሞ፣ ለማስታወስ ያህል፡ ባለፈው ነሐሴ እንደተነገረው፡ ዩኒቨርሲቲዎች ለፓርቲው ፖለቲካዊና ርዕዮተ ዓለማዊ ተገዥ ያልሆኑትን ተማሪዎች ተቀብለው አንዳያሰተምሩ መከልከሉ፡ ትምህርት ለመስጠትም በራቸውን የሚከፍቱበትን ቀን ሳይቀር ገዥው ፓርቲና ትምህርት ሚኒስቴር የሚወስኑበት ሁኔታ መፈጠሩ፡ የዩኒቨርስቲዎቻችን ራስ ገዝነት ደብዛ ማጥፋትና የሚስጡት ትምህርት መሪዎቹ ራሳቸው በቅጡ ባልሰነቁት ርዕዮተ ዓለም መጨመላለቁ፣ ምን ያህል የትምህርትን ምንነንት ያጎድፈና ዕውቀትን የሚጻረር ድርጊት መሆኑ ሊሠመርበት ይገባል።
በአጠቃላይ፡ በተለይም ከሐምሌ 2014 ጀምሮ በከፍተኛ የትምህርት ተቋሞች ሲካሄድ የነበረው እጅግ ተቃውሞ የበዛበት፣ ሕዝብ የተፋውን የገዥውን ፓርቲ ፖለቲካና ርዕዮተ ዓለማዊ አመለካከትና የታሪክ ጥገና በስነጋ ለመጋትና መድረኩም በአብዛኛው ጸረ-ኢትዮጵያ ታሪክና ጸረ-ኢትዮጵያዊነት እንዲሆን በተደጋጋሚ የተደረጉ ጥረቶችን ቀለማቸውን ባልለወጡ የኢትዮጵያ ልጆች በሃገራችን ላይ ስለተቃጣው ደባ ምንነትና ጥልቀት ለወጣቶቻችንና ለኢትዮጵያ ሆኖ ጥሩ ግንዛቤ የሚፈጥር መልካም አጋጣሚ ሆኖላቸዋል።