Wednesday, December 3, 2014

‘የወያኔ ወንጀለኛ ባለሥልጣናት የእጃቸውን ያገኛሉ!’’

የቀድሞው የወያኔ ከፍተኛ ባለሥልጣን እና የትግራይ አስተዳዳሪ ፤ የአሁኑ አረና የተባለው
ድርጅት መሪ ገብሩ አሥራት ፤ የኢሕአፓ አመራር አባላት የነበሩት እነ ጸጋዬ ገብረመድህን እና
ነባር አባላቱ ከዘሬ 23 ዓመታት በፊት መገደላቸውን ይህንኑንም በቅርቡ በጻፈው መጽሐፉ
መግለጹን ለአሜሪካ ድመጽ ሬዲዮ የአማርኛው ክፍል በሰጠው ቃለ-ምልልስ ገለጸ፡፡
እነዚህ ለሕዝባቸው እና ለሀገራቸው ራሳቸውን አሳልፈው በመስጠት አስከፊውን የደርግ አገዛዝ
ሲታገሉ የነበሩ ብርቅዬ የሕዝብ ልጆች የተገደሉት ፤ በወያኔ ፍርድ መሆኑን ገብሩ አስራት
ገልጿል። የሞት ፈርዱን የወሰኑትም ፤ ሟቹ መለስ ዜናዊ ፤ ስዬ አብርሃ ፤ ተወልደ ወልደ ብርሃን
፤ በረከት ስምኦን ፤ አባይ ጸሐዬ ፤ አለምሰገድ ገብረአምላክ እና ሀየሎም አርአያ መሆናቸው
የታወቀ ሲሆን ፤ እሱ ግን በፍርድ ሂደቱ ላይ እንደሌለበት ተናግሯል፡፡
ይህንኑ ተከትሎ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ጠንከር ያለ መግለጫ ያወጣ ሲሆን ፤
መግለጫው “እነዚህ ወንጀለኞች ለፍርድ ቀርበው የእጃቸውን ማግኘት አለባቸው” ብሏል፡፡
ጸጋዬ ገብረመድህንን ጨምሮ ሌሎች ነባር የኢሕአፓ አባላት በወያኔ እጅ የወደቁት ፤ ወያኔ አዲስ
አበባን ከመቆጣጠሩ በፊት ከሻዕብያ ፣ ከሱዳን እና ከሌሎች ባዕዳን አገሮች ጋር በመተባበር
በኢሕአፓ ሠራዊት ላይ በከፈቱት ከፍተኛ ውጊያ ወቅት መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡

ኢሕአፓ

http://www.eprp.com/EthiopiaGazeta/Ethiopia-Newspaper-Tiqmt_Hidar-3gnaAmet-2007.pdf